Home » Articles » ሲደክም ከዋለ መብሉ የታለ?

ሲደክም ከዋለ መብሉ የታለ?

ሰላማዊት ጌታቸው

 

መሪ ጥቅስ፡ – ” የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።”

(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6)

የመልእክ ዋና ሐሳብ ፦ “የግብርናውን ወቅት ለይቶ በማወቅ፣ ሥራው የሚጠይቀውን ተግዳሮት በቁርጠኝነት

በመቋቋም ዘርቶ አርሞና ከክፉ ጠብቆ የሚያሳድግ ገበሬ የመጀመሪያው በላተኛ እንደሚሆን ሁሉ በአገልግሎቱ

የሚደክም/የሚተጋ አገልጋይ የአገልግሎቱ ፍሬ ቀዳሚ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል”

ጳውሎስ ጠሊቅ መካሪ ነው ። ጢሞቴዎስን ሲመክረው ከተጠቀማቸው ምሳሌዎች ውስጥ ወታደር ሯጭ ገበሬ የሚሉት ጥልቅ ሃሳብ የያዙ ናቸው!! የሚደክም ገበሬ ማለት ምን ማለት ነው!? ገበሬ በራሱ ትርጓሜው ምንድነው!?

ገበሬ ማለት ….

[[.ጥማድ በሮችን ጠምዶ ምድርን የሚ ዐርስ ገበሬ ዘርን የሚዘራ።]] [[በግዕዙ ደግሞ

ሐራሲ ፣ መስተገብር ፣ ዲራግቦ]]

OROMIFFA

noun

qonnaan bulaa, qonnaan jiraataa, qotee bulaa, qottuu, nama oyruu qotu

[ቆናን ቡላ፣ ቆናን ጂራታ፣ ቆቴ ቡላ፣ ቆቱ፣ ነመ ኦይሩ ቆቱ]

ከላይ ሃሳቤን ይዤ ስንደረደር ጳውሎስ ጠሊቅ መካሪ ነው ብያለሁ !! ምክንያቱም የግብርናን ውጣ ውረድ ያየ ይመስለኛል። አገርልግሎትን በግብርና መስሎ ታማኝ ልጁን ሲመክር የምናየው!! እስኪ ጳውሎስ ያየበትን መንገድ እንደተረዳሁት ላስቀምጥ!

 

1ኛ. ገበሬ ወቅት ያያል የሚመነጥርበትን የሚያርስበትን የሚዘራበትን የሚያርምበትን የሚኮኩከትበትን አዝመራው ሲደርስ ከወፎች እንዴት አዝመራውን መከላከል እንዳለበት ወቅቶችን በቅደም ተከተል ያውቃል!!

እንግዲያውስ የአዲስ ኪዳን አገልጋይ ወቅት እና ቦታ ይመርጣል ይጠብቃል አርቆ ማየት አለበት ዛሬ የሚመነጥረው የአገልግሎት ጅማሮ ነገ ምን ያይስታቅፈው እንደሆነ አርቆ ማየት መናፈቅ አለበት! ከመመንጠር እስከ መታቀፍ ወይም ወደ ጎተራ እስከ ማስገባት ድረስ ያለውን ትግል ለመታገል መድረሻውን ውጤቱን አርቆ ማየት አለበት!!

 

2ኛ. መጀመር አለበት ገበሬ የእርሻ ወቅት እንደደረሰ ካወቀ በመመንጠር ይጀምራል። ለዚህም ይመስለኛል የሃገሬ ነገር አዋቂዎች “”ለካህን ጥምቀት ለገበሬ ግንቦት” ይላሉ

ስዚህም ብርቱ አገልጋይ ቁጭ ብሎ በማየት ብቻ አይቦዝንም ተነስቶ ስራን ይጀምራል። ከባድ የሚባል ትግል ለመጀመር እርፍ የሚባል ነገር መያዝ አለ ማረስ መጎተት ይህን ሁሉ በተግባር መሞከር አለበት!! የሰማውን ስለ ተሰቀለው ክርስቶስ ለመስበክ የታጠቀ መሆን አለበት! አለበለዚያ “”ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል “” እንዲል የሃገሬ ሰው።

አቅሙና ብርታቱ በጌታ ፀጋ የሆነለት ባርያ ያየውን ለመያዝ ለመውረስ መመንጠር አልፊ እና አንገላች ቢሆንም ግን በፀጋው ተደግፎ እርፉን አጥብቆ መያዝ አለበት!!!

 

3ኛ. በእርሻ ወቅት የሚከሰቱ አንዳንድ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም እራሱን ማሳመን አለበት!! ለምሳሌ ዶፍ ዝናብ ገበሬን ከማበስበስ አልፎ የአረሰውንም መሬት አፈር ሊጠርግ የሚችል ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል።

ያንን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ድጋሚ አርሰዋለሁ ብሎ እራሱን ማሳመን አለበት!!

ስለዚህ አንድ አገልጋይ በአገልግሎት ውስጥ እጅግ ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ ተግዳሮቶች ሊከብቡት ይችላሉ ሊጥሉትም ይችላሉ ስለዚህ በፀጋው እንዲደግደፈው እግዚያብሔርን እንደ ባርያም እንደ ልጅም በንሰሃ እና በምስጋና እየተማፀነ መበርታት አለበት! !! በታሃድሶ ዳግም ወደ አገልግሎቱ መመለስ ይኖርበታል።

ሌላው ሊገጥመው የሚችለው ተግዳሮት የጭቃ ውስጥ እሾህ ነው! የጭቃ ውስጥ እሾህ በሚለሰልስ እና ለመገግጥ በሚያመች ጭቃ ውስጥ በድብቅ የሚወጋ እሾህ አለ!! ስለዚህ ገበሬው እሾህን በእሾህ እንደሚባል እሾሁ ህመም እየፈጠረ ቂም ሳይዝ ማውጣት አለበት!!

ብርቱ አገልጋይ በአገልግሎት ህይወት ውስጥ ሰው ሊያስተው ሊጎዳው እና በእጅጉ ልቡን ሊሰብረው ይችላል። ይህንን አይነት ነገር ሲከሰት ፍቅር በሚባል መዳኒት ራሱን ማከም አለበት!!

 

4ኛ. ብርቱ ገበሬ ያርማል። የዘራውም ዘር ስር ሰዶ ቡቃያው ብቅ ሲል አንዳንድ አረሞች አብረው ተመሳስለው መብቀላቸው አይቀርም። ስለዚህ የተዘራው ዘር ፍሬ ነቅጡ እንዲያፈራ ያገባኛል በሚል እምነት አረም መነቀል አለበት!! አለበለዚያ እጩጭ ሆኖ ለምግብነትም የሚውለው ያን ያህል አይሆንም!! ስለዚ ብርቱ አገልጋይ በአገልግሎቱ ያሳደጋቸው የእግዝያብሔርን ቃል የዘራባቸው ደቀ-መዛሙርት አንዳንድ የሚነቀል ከባህሪም ሆነ ከተለያዩ ነገሮ ሊያርም ይገባል!!። የትኛውም አገልጋይ በየትኛውም ሁኔታ ስለ ወንድሜ ያገባኛል ሊል ይገባል እራሱን አካል አድርጎ ካላመነ አካል ነን እያለ የሚያስተምረው ትምህርት አልገባውም ማለት ነው። ስለዚህም ያገባኛል በጣም አስፈላጊ ባህሪ ነው። አለዚያ እንደ ኤሊ ልጆች የሰነፍ ልጅ ሰነፍ ያስብሉታል!! መምከር መገሰፅ መከባከብ የአንድ አገልጋይ ድርሻ ነው ብዬ አምናለሁ!!

 

5ኛ. መጠብቅ አለበት አንደ ገበሬ የዘራው ዘር ቡቃያው ደርሶ አዝመራው ፍሬ አፍርቶ ሲያሼት ከተለያዩ አዋፋትና እንስሳት መጠበቅ አለበት አለዛ የዘራው ዘር የጎመጀለት እሸት ተቦጥቡጦ ትራፊ ይደርሰዋል!!

ብርቱ አገልጋይም የእግዝያብሔር ቃል አስተምሮ እና መግቦ ያሳደገውን ሰው ሊጠነቀቅለት ይገባል። ከእግዝያብሔር ሃሳብ ሊወጡት የሚችሉ ተግዳሮቶች ሲመለከት ሊታገልለት ይገባል ካልተጋደለለት እስካሁን የለፋው ልፋት ከእቁብ አልቆጠረውም ማለት ነው!!

ስለዚህ መጋደል ሌላኛው የብርቱ አገልጋይ መገለጫው ነው!!

 

6ኛ. ዋናው እና ብዙ ልፋት የተለፋበት አላማ ምንድነው ካልን እህል ለማግኘት ነው። ለመብላት ለማብላት ማለት ነው ።

የሃገሬ ገበሬ ልክ ታህሳስ ላይ የመጀመሪያውን ወቅ ወቅቶ ሲያስገባ እንዲህ ይላል ” አመት አመት አድርሰኝ” ይላል እዚህ ጋር እኔ ይሄን እረዳለሁ ቢያንስ ለከርሞ በእግዝያብሔር ተስፋ አድርጓል ዘንድሮም ያሳለፈው እሱ እንደሆነ አምኗል!!

ብርቱ የአዲስ ኪዳን አገልጋይም የየትኛውም የከፍታ ጥግ ይደረስ እግዚአብሔር እንዳደረሰው ከእርሱ አንዳች እንዳልሆነ በመረዳት ማመስገን አለበት ያመነው አምላክ ውሸታም እንዳልሆነ ለራሱም ለሌሎችም መመስከር አለበት!!

ለሚቀጥለውም እግዚአብሔር በፀጋው እንዲደግፈው በይበልጥ ለማምረት እሱ የሙጥኝ ማለት አለበት!!

ሌላው ሲጓጓለት የነበረው አዝመራ ደርሶ ነዶ ከማሳ ታቅፎ ከአውድማ እግዞ ጎተራ ሲከት በቃ ከበሬ ግቡን መታ ማለት ነው!! ይሄኔ ገበሬው ከዘራው ላይ የሚመገብም ነው የሚመግብም ነው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን የምትመገብ የምትመግብ ይለዋል የትኛውም አገልጋይ ተመጋቢ ነው ካልታመገበ መመገብ አይችልም !!

ሌላው እና የመጨረሻው ለከርሞ ዘር ያስቀምጣል

ብርቱ አገልጋይም በአስተማራቸው ውስጥ ከእየሱስ የሆንውን እውነተኛ ፍቅር ትህትናን እና ታዛዥነትን በእነርሱ ውስጥ ሊያስቀምጥ ግድ ይለዋል!!!!

ከሁሉ በላይ ፅናት የብርቱዎች ካባ ናት መፅናት በየትኛውም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ጭላንጭል ተስፋ እንኳን ባለበት ፅናት አርቆ ማያ መነፅር ናት !!!

ዛሬ አካላችን ቆሞ አምሮአችን በብዙ መንገላታትን ውስጥ ብንሆንም ጌታን ብቻ እያየን እርሱን ብቻ እየታመንን ከሄድን ፅናት አለን አለዛ አምናንሃል የምንለው እግዚአብሔርን አላመነውም ማለት ነው !!

ታማኝ ባርያ ነህ!?

ታማኝ ባርያ ነሽ !?

ፅና ፅኚ ፅኑ!!!!~

በመጨረሻም ፀሎት!!

በኪነ-ጥበብህ እና በሃያልነትህ ሰማይን የዘረጋህ ምድርን ያፀናህ እሩህሩህና ደግ አባት እግዚአብሔር ሆይ ስም የተመሰገ ነው ሃያልነትህ እሙን ነው። አንተ ብርቱ እሩህሩህ እና እውነተኛ አምላክ ነህ!! ማደሪያህ ዙፋንህ በምስግልናችን ይሞላ። ታላቅ ሆነህ ሳለ ማንንም የምትንቅ ሁሉን በእኩል አይንህ የምታይ፤ ሁሉን በአንድ አይነት ፍቅር የምትወድድ፤ ልጅህን እስከመስጠት የወደድኸን እና ለቤትህ ባርያ አድርገህ ልጆችህን የምትሾም ትሁቱ አላክ እግዚያብሔር ሆይ እናመሰግንሃለን!!!

አባት ሆይ ታማኝ ባርያዎችህ እንሆን ዘንድ እባክህ ፀጋህን አብዛልን አንተን በመፍራት ክብርህን በማየት እና ሁሉን ለክብርህ እዲሆን በመመኘት ወደ ዙፋንህ መቅረብ እንዲሆንልን ለመንኹ!! እነሆ ሰምተህ እሺ እንደምትለኝ አመንኹ ክብር ይሁንልህ!!! ሁሉ ከአንተ በአንተ ለአንተ የሆነው ሁሉ ሆነ የሚሆነውም ይሆናል። በሁሉ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተመስገን ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን አሜን!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

x

Check Also

Fikadu Borena Week Four

Related

%d bloggers like this: