Home » Articles

Articles

አባቶች ሲስቱስ?

ወጣቱ ለአዲስ ነገር ያለውን ጥማት በማየት “ቅልብልብ፣ ለስሕተት አሠራር ክፍት፣ ለቋሚና ዘላቂ ነገር ራሱን የማይሰጥና ተለዋዋጭ” አድርጎ የማየት አዝማሚያ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ የዚህች አጭር ምልከታ ዐላማ፣ የወጣቱን መንፈሳዊ ጤንነትና አካሄድ ማጠየቅ ሳይሆን፣ በዕድሜ ስለጠኑ ግን ደግሞ እውነትን ስለተቀሙ፣ በዘመን ዕድሜ ቆይታ የእውነትን መንፈስ አውልቀው ሐሰትንና አሠራሩን በአጭር ስለታጠቁ፣ በቊጥርም እየበዙ ስላሉ፣ ስለ “ትናንት አባቶች” የዛሬ ስሑታን ...

Read More »

“Athanasius Contra Mundum” – Athanasius Against the World by Fitsuman Girma

“Athanasius Contra Mundum” – Athanasius Against the World (ማሳሰቢያ፡- ‹ረዥም ጽሁፍ› እንዲሉ የፌስቡክ ጦማሪዎች 😉) በዚህ ወር (በፈረንጆች May አጋማሽ ላይ) አንድ ትልቅ የቤተ ክርስቲያን አባት የሚታወስበት ወቅት ነው። ያኔ ክርስትና ገና እንደ አዲስ እምነት በየቦታው እየተንሰራፋ ባለበት በግብጽ አሌክሳንደሪያ ከ296 – 298 ዓ.ም አከባቢ እንደተወለደ ይታመናል። ወቅቱ የክርስትና ቀኖና እና አስተምህሮዎች እንዳኹኑ ዘመን በውል ተሰድረው ያልተጠናቀቁበትና ብዙ መሰረታዊ የክርስትና ሃሳቦች ...

Read More »

ታላቁ ወንጀል! (Sola Scriptura ስንል…..)

በአሳየኸኝ ለገሰ   ሀደን ሮቢንሰን የተባሉ ጸሐፊ፣ ቅዱሱ መጽሐፍ ላይ ከሚፈጸሙ እጅግ የከፉ ወንጀሎች ‹‹ዋነኛው ነው›› ያሉትን ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ፤ “በርካታ ሰባኪያን፣ ለስብከት ወደ ምስባኩ ሲወጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው ነው፡፡ ስብከታቸውን ሲጀምሩም ከዛው መጽሐፍ ላይ አንብበው ነው፡፡ የሚሰብኩት ሲፈተሽ ግን (ባነበቡት ክፍል ውስጥ) መጽሐፉ ሊል የፈለገው ሳይሆን፣ ሰባኪዎቹ ሊሉ የፈለጉት ሆኖ ይገኛል፡፡ መጽሐፉን ገልጠው የሚያነቡትም የሕዝቡን ጆሮ ለመሳብ፣ እንደ ‹አፒታይዘር› ...

Read More »

የእውቀት እና የእውነት መልክ

በአሹቲ ገዛኸኝ   ክቡድ በሆነው ምሽት ላይ “ሰውየውን በሕይወት እና በሞት መካከል ደብድበውት ጠፉ” ይለናል፣ የክርስቶስን ምሳሌ እያስታወሰ የሉቃስ ወንጌሉ ፀሐፊ ሉቃስ (ዶ/ር)።   መቼም እንደ ካህን በሌሊት የሚነሳ ያለ አይመስለኝም። ይቀድሳል፣ ያስቀድሳልና። እናማ ጎበዙ ካህን ስብከቱን ሰርቶ በሌሊቱ ዘው ዘው እያለ፣ ምናልባትም እኮ ይሄኔ  “እግዚአብሔር ያነሳል” የሚል ስብከቱን በእጁ ይዞ ይሆናል። ወንበዴዎችም የደበደቡት ያ ምስኪን ደሙ እላዩ ላይ እንደተዝረበረበ ...

Read More »

ሰው፣ ኃጢአትና የእግዚአብሄር መፍትሄ

በአሌክስ ዘፀአት   የኃጥአትና የኃጥተኝነት ምንጩ የስነ-ምግባር ችግር አይደም ፣ የወረስነው ዘር (Sin Seed) እንጂ፡፡  በስነ-መለኮት የመጀመሪያው ኃጢአት (Orgional Sin) የሚባል ነገር አለ፡፡ ያ ኃጢአት የሰው ሁሉ አባት የሆነው አዳም ያደረገው የመጀመሪያ ኃጢአት ነው፡፡ አዳም በዲያብሎስ በተታለለና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በተላለፈ ጊዜ ወደ ማንነቱ ውስጥ የአመጽ ዘር ገባበት፡፡ እንደ ሐዋሪያው ቅዱስ ዮሐንስ ገለጻ ከሆነ ኃጢአት የተጀመረው በአመጽ ነው፡፡ “አመጽ ኃጢአት ነው፡፡” ...

Read More »

ሐሰተኞችን እስከምን ድረስ እንታገሳቸው?

ክፍል ሁለት ፍጹማን ግርማ በመጀመሪው “ሐሰተኞችን እስከምን ድረስ እንታገሳቸው?” በሚል ርዕስ በተጻፈው ጽሁፍ ውስጥ፣ የሳቱትን አገልጋዩች ለመከላከል በሚል በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱ ጥቅሶችና አመለካከቶች የተወሰኑትን ለማየት ሞክረን ነበር። የተጠቀሱትን ሁለቱን ነጥቦች ለማስታወስ ያክል፡- 1-” እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ” 2- “ሐሰተኞችን ስማቸው ሳይጠቀስ በደፈናው እንቃወም” የሚሉ ነበሩ በዚህ ጽሁፍ ከተለመዱት የመከላከያ አባባሎች ሶስተኛውን እንመለከታለን። 3- “እኔ የሃሰት አስተምህሮንና ልምምድ የመለየት ፀጋው አልተሰጠኝም፤ ስለዚህ የኔ ድርሻ ...

Read More »

ሐሰተኞችን እስከምን ድረስ እንታገሳቸው?

ክፍል አንድ ፍጹማን ግርማ   የክርስቶስን ወንጌል ሰባኪዎች እንዳሉ ሁሉ ልዩ ወንጌል ሰባኪዎችም አሉ፤ እውነተኛ ነቢያት እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያትም አሉ፤ እውነተኛ አስተማሪዎች እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ አስተማሪዎችም አሉ። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ፈተና ከሆኑት መካከል የስሕተት ትምህርትና እንግዳ ልምምዶች መሆናቸው ተደጋግሞ በመነገር ላይ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት የኑፋቄ ትምህርቶችና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት የጎደላቸው ልምምዶች የአብያተ ክርስቲያናት ...

Read More »

ዊል ስሚዝ እና ቅዱስ ጳውሎስ

ዊል ስሚዝ እና ቅዱስ ጳውሎስ በአሹቲ ገዛኸኝ ለፊልም ብዙ ትኩረት የለኝም፣ ካየሁም መርጬ ባይ ነው የምሻው። እናም መርጬ ካየኃቸው ፊልሞች ውስጥ “The pursuit of happines” የሚለውን ዊል ስሚዝ የሚሰራበትን ፊልም በጣም እወድለታለው። አቤት ትወና! እውነት ለመናገር በእሱ የእድሜ ደረጃ እንደዚህ ግሩም አድርጎ የሚተውን አላየሁም፣ አይቻለው እንዴ? አይመስለኝም። ይህ ብቃቱ ያሳመናቸውም ፈረንጆቹ “የጥቁር ፈርጥ” ይሉታል። በእርግጥ እኔም እስማማለው “የጥቁር ፈርጥ ዊል ...

Read More »